News

በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ቀለም የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር

      የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በሚያዘጋጀው ቀለም የጥያቄ እና መልስ  ውድድር ተሳታፊ የሆኑ ተማሪዎቻችን እንዲሁም የት/ትቤቱ አስተዳደር በፕሮግራሙ የ2016 የመክፈቻ ስነ ስርዓት በEBC ስቱድዮ ተሳትፈዋል። በመክፈቻ ፕሮግራሙም ላይ የት/ትቤታችን አስተዳደር የሆኑት አቶ ጀምበሬ ጣፋ አጭር ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም ከተለያዩ ት/ትቤቶች ለውድድሩ ተመርጠው ለመጡ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልክት አስተላልፈዋል ለተወዳዳሪ ተማሪዎችም መልካም እድል ተመኝተዋል። ከ አቶ ጀምበሬ ጣፋ በመቀጠልም የ6ኛ ክፍል የውድድሩ ተሳታፊ ተማሪያችን ኬቤክ ጀምበሬ አጭር ንግግር አድርጋለች። ምሉ ቪዲዮዉን በተከታዩ ድረገፅ ይመልከቱ Click here for full Video

የልጆች ቀን በትጋት ቁ.1 እና 2 በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

      ዛሬ ታህሳስ  26/2016 ዓም  በትጋት ቅድመ መደበኛ  ቁጥር 1 እና ቁ.2 የልጆች ቀን በደማቁ ሁኔታ ተከብሯል። ጎዳና ከሚኖሩ አቅመ ደካሞች ጋር እንዲሁም ኑሯቸውን ጎዳና ላደረጉ የልጆቻችን እኩያዎች የማልበስ እና ምሳ የማጋራት ስራም ተሰርቷል።ሁሉም ልጆቻችን ደስ በሚል ሁኔታ አክብረውታል። 

እጅግ በጣም ታላቅ የምስራች

       ተማሪዎቻችን በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከ እና በወረዳ 01 ስር ካሉ የመንግስትም ሆነ የግል አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መካከል በተካሄዱ የተለያዩ ውድድሮች እጅግ በጣም ከፍተኛ ውጤት በማምጣታቸው እንኳን ደስ አላችሁ።

የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክበብ አባላት ፕሮግራም

     ዛሬ ታህሳስ 12፣ 2016ዓ.ም በትጋት ቁጥር 1 እና 2 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት  የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክበብ አባለት የቀረበ አስደናቂ ፕሮግራም ። አስተባባሪ መምህራን ፣ ፕሮግራም አቅራቢ ተማሪዎች ታዳሚዎችን ከልብ እናመሰግናለን ።